ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን የአብርኾት ቤተመጽሐፍት :መስቀል አደባባይ : የማዘጋጃ ቤት ህንፃ እድሳትን :ሸገር ቁጥር ሁለት: የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሙዚየምን ጨምሮ ሌሎችንም አገልግሎት እየሰጡ ያሉና ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶችን አስጎብኝተዋል።እየተጎበኙ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ሃሳብ አመንጪነት ና አመራር ሰጭነት በአጭር ግዜ የግንባታ ስራቸው ተጠናቆ ለሕዝባዊ አገልግሎት ክፍት የተደረጉ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን አመራሩ በዚሁ ልክ በትኩረት ስራዎችን መጀመርና መጠናቀቅን ባሕል ማድረግ አለበት ተብሏል ።
በጉብኝቱ ወቅት አስተያየታቸውን የሰጡት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ብልፅግና ሰው ተኮር ነው የምንለው ፤ በርካቶችን ተጠቃሚ ማድረግ የቻሉ ፕሮጀክቶችን ነው ተግባራዊ ያደረግነው ብለዋል፡፡የምገባ ማእከላት አሁን ካሉት ስድስት በተጨማሪ አስተዳደሩ ሌሎች ስድስት በቅርብ ጊዜ ገንብቶ አጠናቆ አስራ ሁለት የምገባ ማእከላት ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልፀው የትኛውም የኑሮ ጫና ያለበት በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የማይችል ማንኛውም የከተማችን ነዋሪ ሄዶ የሚመገብባቸው ይሆናሉም ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የከተማው ህዝብ ካስተባበሩት መልካም ህዝብ መሆኑን አዲስ አበባ ማሳያ ናት ያሉ ሲሆን ባለፉት ወራት ከህብረተሰቡ አንድ ቢሊየን ብር በማእድ ማጋራት ሰብስበን ህብረተሰቡ መድረስ የሚችልበት ሲሆን ወደ ሰባት ቢሊየን የሚሆን ደግሞ በድርቁም ለተፈናቀሉም በማዋጣት አብሮነቱን ያረጋገጠበትም ጭምር ነው ብለዋል፡፡በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ በከተማና በሀገር አቀፍ ደረጃ ፤በግንባታ ሥራ ላይ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶችና ሌሎችንም በየደረጃው የሚገኙ ፕሮጀክቶችን በጥብቅ ክትትል መርቶ በማጠናቀቅ ፤ በተያዘላቸው የግዜ ገደብ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ፤ የተገልጋዩን ሕዝብ እርካታ ማሳደግ እንደሚገባ ተጠቁሟል ።