ከመላው የሀገራችን ክፍሎች ለተውጣጡ የመንግሥት አመራሮች በሚሰጠው ስልጠና ላይ ለመሳተፍ በደቡብ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ወላይታሶዶ ተገኝቻለሁ ፤ የሶዶ እና አካባቢው ማህበረሰብ ላደረገልኝ ደማቅ አቀባበል ከልብ አመሰግናለሁ::

መንግስታችን በ17 ማዕከላት ስልጠና በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ፤ስልጠናው የአመራሩን የአመለካከትና የተግባር አንድነትን አስጠብቆ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና እና የሀገረ መንግስት ግንባታ ጉዞ የሚያሳኩ ጉዳዮችን ተረድቶ ፣በጋራ ለመተግበርና የትናንት ወረትን ወደ ዛሬና ነገ ምንዳ ለማሸጋገር አቅም ለመገንባት የሚያስችል ይሆናል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Share this Post