የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር አደረገ!

 

የከተማ አስተዳደሩ ከግሉ ዘርፍ ጋር በጋራ በመተባበር ከተማውን ለማልማት በሚያስችለው መንገድ ዙርያ በዛሬው እለት ውይይት አካሂዷል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ት ያስሚን ዉሀቢረቢ የከተማ አስተዳደሩ ያዘጋጃቸውን አማራጭ የቤት ልማት ሞዳሊቶችን ለውይይት መነሻ ይሆን ዘንድ ለሪል እስቴት አልሚ ድርጅቶች ተወክለው ለመጡ ተሰብሳቢዎች አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ከንቲባ አዳነች በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር በመተባበር ፣የሚችሉ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግና ሌሎችም በአቅማቸው ልክ ቤቶቹ ተገንብተው በተመጣጣኝ ዋጋ ተከራይተው የሚኖሩበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ከተማ አስተዳደሩ ከሚመለከታቸው ሁሉ ጋር የላቀ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀዋል፡፡

ባለሀብቶች የልማት አጋር እንደመሆናችሁ መጠን የተዘጋጁ ሞዳሊቲዎችን በዝርዝር በመመልከት ለተግባራዊነቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በቅንጅት ለመስራት እንቅስቃሴ ልታደርጉ ይገባል ብለዋል አያይዘውም የከተማ አስተዳደሩ ፤የነዋሪዎችን የቤት ፍላጎት በሂደት ለመቅረፍ አምስት የቤት ግንባታ ሞዳሊቲዎችን በዝርዝር አዘጋጅቶ ለተግባራዊነቱ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ አጋርነታችሁን እየተጠባበቀ የሚገኝ በመሆኑ እናንተም በነፍስ ወከፍ በአጭር ግዜ ግንባታ ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማምጣት የየድርሻችሁን አሻራ ለማኖርና የታሪክ ተከፋይ ለመሆን ልትሰወስኑ ይገባል ሲሉ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የውጭ አገር አልሚዎችን የአዋጭነት ደረጃን በመፈተሽ እንዲሳተፉ ለማድረግ ይሰራልም ብለዋል ከንቲባዋ

የቤት አቅርቦትን በሚፈለገው መልኩ ተደራሽ ለማድረግ በዓመት 200,000 ሺና ከዚያ በላይ ቤቶችን መገንባት ያስፈልጋል ያሉት በምክትል ከንቲባ መዓረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ት ያስሚን አሁን ያለው ወቅታዊ ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ አልሚዎች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በጋራ የተዘረጉ ሞዳሊትዎችን መሠረት በማድረግ ልትሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

የግሉ ዘርፉ በተለይ የቤት ልማትን በሚመለከት የፌደራል መንግስትና ከተማ አስተዳደሩ የጀመሩትን በርካታ የማክሮ ኢኮኖሚ የለውጥ ስራዎች መሠረት በማድረግ በሽርክናና በሌሎችም ተስማሚ አማራጮች ዘርፉን የማነቃቃት ሥራ መስራት ከአልሚዎች ይጠበቃል ሲሉ አስታውቀዋል ኃላፊዋ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በጋራ በቅርበት የሚሰራ ግብርሃይል በውይይቱ መጨረሻ ተቋቁሟል በውይይቱ ማጠቃለያ ተሳታፊዎቹ የማዘጋጃ ቤትን እድሳት ተዟዙረው ጎብኝተዋል፡፡

Share this Post