ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ በጥቂት ግዜ የሚጠናቀቁ ሰዉ ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን አስጀመሩ።

 

ሠው ተኮር የሆኑ አቅመ ደካሞችን ተጠቃሚ የሚያደረጉ 4 ባለ 9 ወለል ህንጻዎች የቤት ግንባታ፡ የምገባ ማዕከል ግንባታ ፥ የከተማ ግብርና ፥ 200 ቤቶችን በክረምት በጐ ፈቃድ ማደስ ፥ የዳቦ አቅርቦትን ለማሳደግ የሚየስችል ግንባታ ፥ ከተጀመሩት ፕሮጀክቶች ውስጥ ናቸው።

በፕሮጀክቱ ማስጀመር መርሃ ግብር ላይ ንግግር የደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሁላችንም : ሌት ተቀን ከሰራን ለውጥ ማምጣት እንችላለን ብለዋል።

ለለውጥ የቆመ መንግሥት ፥ ትጉህ ህብረተሰብ እና ባለሃብት ስላለን ካስተባበርነው የምንፈልገውን ለውጥ ማምጣት እንችላለን ሲሉም ገልፀዋል::

ኢትዮጵያዊነታች ከወደድን አቅመ ደካሞችን እየደገፈን ፥ መብላት የማይችሉት እንዲበሉ እያገዝን ፥ ተበብረን ለለውጥ መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።ለውጥ የትጋት ውጤት ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፥ ሁሉም የከተማችን ነዋሪዎች ተግተው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል :: የጎሮ አትክልት በማልማት፡ አካባቢን በማፅዳት ከተማችን ውብና ምቹ እንድትሆን ማድረግ ይጠበቅብናል::

ከተማችን የዲፕሎማቲክ ማዕከል ሆና ደረጃዋን የጠበቀች በውበትዋም በፅዳቱም ማራኪ መሆን ይጠበቅባታል : በዚህም በቅርቡ የጀመርናቸው የከተማችን ደረጃዋን የሚያሳድጉ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።በአጭር ጊዜ በከተማችን ሞዴል ሥራዎችን ለመሥራት ከጎናችን ለሆኑት ምስጋና አቅርበዋል ::

አቶ ጀማል አህመድ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሃላፊ ሚድሮክ ለድርጅቱ 2ኛ የሆነ ምገባ ማዕከል ግንባታና በክፍለ ከተማው ዛሬ ከተጀመሩት 4 ህንፃዎች አንዱን እንደሚገነቡ ገልፀዋል። ሚድሮክ ኩባንያ የመንግስትን ጥሪዎችን ተቀብሎ በልማቱ እየተስተፈ የሚገኝ ፧ በቀጣይም ከመንግስት ጒን ሆነን እንሰራለን ብለዋል።አቶ ደርቤ አሰፋው የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሃለፊ እኛ ከተባበርን የከተማችን ውበት ማሳደግ እንችላለን ብለዋል። የአሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ የኮርፖሬት ሃላፊነቱን ለመመጣት በተለያዩ መስኮች እየሰራ መሆኑን ገልፀው ዛሬም አቅመደካሞችን ተጠቃሚ የሚያደርገው አንዱን ህንጻ ለመገንባት ቃል ገብተዋል።

Share this Post