ለከተማችን ነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ለመፍጠር እንተጋለን፣ በቃላችን መሰረትም እንፈፅማለን" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

 

ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክ/ከተማ የ35 አባወራዎችን ቤት ግንባታ አስጀመሩ።

ከንቲባ አዳነች የቤት ግንባታውን ባስጀመሩበት ወቅት ለነዋሪዎቹ እንደተናገሩት እነዚህን ቤቶች ማስገንባት ከመጀመራችን በፊት ሰው መራብ የለበትምና ለነዋሪዎቹ የሚሆን የዳቦ ማምረቻና ለአቅመ ደካሞች የምገባ ማዕከል እያስገነቡ መሆናቸውን ጠቅሰው ከነዚህም በተጨማሪ 90 ቤቶችን በማስገንባት ለማስረከብ እየተዘጋጀን ነው ብለዋል።

 

በዛሬው ዕለት የሚጀመሩት ተጨማሪ ቤቶችም በሁለት ወራት ውስጥ ተገንብተው ለቤቶቹ ባለቤቶች የሚረከቡ መሆናቸውንም ክብርት ከንቲባዋ ተናግረዋል

ለከተማችን ነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ለመፍጠር እንተጋለን ያሉት ከንቲባዋ በቃላችን መሰረትም ፈፅመን ወደ ሌሎች ግንባታዎች እንሸጋገራለን ብለዋል::በዛሬው ዕለት የተጀመረው የቤት ግንባታ በፌዴራል ጉምሩክ ኮሚሽን የሚሰራ ሲሆን ለግንባታው የሚውል 15 ሚሊዮን ብር የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስረክበዋል።

#አዲስ_አበባ እንደ ስሟ አዲስና ውብ እናደርጋታለን!!

 

 

 

 

 

 

Share this Post