ዛሬ ከብሉምበርግ ፊላንትሮፒ የትራፊክ አደጋ ጉዳት ዘርፍ ኃላፍ ከሆኑት ሚስ ኬሊ ላርስን እና አብረዋቸው ከሚሰሩት የወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት እና የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የስራ ኃላፊዎች ጋር በከተማችን የትራፊክ ማኔጂመንት እና ሴፍቲ ስትራቴጂካዊ እንዲሁም ኦፕሬሽናል ጉዳዮች ትብብር ዙሪያ በሰፊው ተወያይተናል።

ከተማችን እስካሁን በዘርፉ ላስመዘገበቻቸው ወጤቶች እና ተምሳሌትነት ያላቸውን አድናቆት ገልጸውልናል። 

ተቋማቱ እስካሁን ላደረጉልን አጋርነት እያመሰገንን፤ ትብብራቸውን ለማሰቀጠል እና ከተማችን በማሳየት ላይ ወደምትገኘው እድገት እና ሽግግር የሚመጥን ደረጃ ለማሳደግ ተስማምተናል። 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Share this Post