29
Jan
2024
ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶች በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንዲቀመጡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያቀረቡትን ጥሪ በመቀበል የጋምቤላ እና የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት ተወካዮች ዛሬ በእጃቸው የሚገኙ ቅርሶችን ለከተማ አስተዳደሩ አስረክበዋል::
ቅርሶቹን የተረከቡት የከንቲባ ጽ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁ ቅርሶቹ ትውልድ የሚማርባቸው ጎብኚዎችና ተመርማሪዎች የሚመራመሩባቸው በመሆናቸው በመታሰቢያ ሙዝየሙ እንዲቀመጡ ሁለቱ ክልሎች ስላበረከቱ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል::