ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተሰጠ መግለጫ

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዘንድሮ ክረምት በጎርፍ አደጋ ስጋት ያለባቸው አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል

አዲስ አበባ ከፈጣን እድገትና ዉበቱዋ ጎን ለጎን ለተለያዩ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ስጋት የተጋለጠች ከተማ እንደመሆንዋ መጠን በባለፉት አመታት የተለያዩ የጐርፍ" የመሬት መንሸራተት"የቆሻሻ መደርመስና መሰል አደጋዎች ተከስተዋል ፡፡ በተለይም ከክረምቱ ወቅት ጋር ተያይዞ በባለፉት አመታት በከተማዋ በወንዝ ዳርቻዎች፣ በተዳፋት ቦታዎች፣ በረባዳማ ስፍራዎችና በሚኖሩ ኗሪዎች ላይ የጎርፍ አደጋና የመሬት መንሸራተት ሁኔታ ከፍተኛ ስጋት ሆኖ ቆይቷል፡፡

በመሆኑም ከተማ አስተዳደሩ በዘንድሮ ክረምት ተመሳሳይ አደጋ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ እንዳያጋጥም ከሚመለከታቸው ተቋማት የባለሙያ ቡድን በማደራጀት የጎርፍ አደጋ ስጋት ያለባቸው ቦታዎች ተለይተዋል። በሁሉም ክ/ከተሞችና ወረዳዎች በተደረገው ጥናት መሰረት 161 ቦታዎችን በተለያየ ደረጃ የሚገለፅ ስጋት ያለባቸው ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 61 ቦታዎች ከፍተኛ የጎርፍ ስጋት ያለባቸው እና ተጋላጭነት ቦታዎች መሆናቸው ተለይተዋል። በጥናቱ ምክረ ሃሳብ መሰረት ከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን የሰው ሀይልና በጀት በመደብ ስጋቱን ለማቃለል ወደ ስራ ገብቷል፡፡

የከተማው አስተዳደር በከተማዉ ነዋሪ ህይወትና ንብረት፣ በተቋማትና በልማት አውታሮች ላይ ዉድመት በሀገራዊ ኢኮኖሚያችን ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ግምት ውስጥ በማስገባት የሚመለከታቸውን ተቋማት በማስተባበር ለአደጋ ተጋላጭ ማህበረሰብና ቦታዎችን በመለየት ከጥናቱ ግኝት ከተሰጡ ምክረ ሃሳቦች በመነሳት ስጋቶቹ እንዲቀረፉ በርካታ ስራዎች እየሰራ ሲሆን

λ በወንዞች ዳርቻ /አቅራቢያ/ የሚኖሩ ማህበረሰቦችን በማንሳት"

λ የወንዞች ዳርቻዎች የድጋፍ ግንብ በመስራት"

λ በወንዝ ውስጥ የተጣሉ ቀሻሻዎችን እና የተደፉ አፈርን በማንሳትና በማጽዳት"

λ የወንዝ ዳርቻዎችን በእጽዋት በመሸፈን"ቱቦዎችን በማፀዳት"

λ የወንዝ ዳርቻዎችን ወሰን በማስከበር የአደጋ ስጋት ለመቀነስ ሰፊ ስራዎች ሰርቷል፡፡

ምንም እንኳን ሰፋፊ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም የተሰሩ ስራዎች በቂ ባለመሆናቸው በተለይም በዘንድሮ አመት የክረምቱ መጠን ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚችል የሚትሮሎጂ መረጃዎች ያስገነዘቡ ስለሆነ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ግብረ-ሃይል በማደራጀት ስጋቱን ለመቀነስ የከተማው አስተዳደር ቀንና ለሊት በመስራት ርብብርብ እያደረገ ቢሆንም አንዳንድ ነዋሪዎች የአደጋ ስጋት ለመቀነስ የሚሰሩ ስራዎችን አዳጋች አድርገውታል።

1. አሁንም ስጋት በሆኑ በተፋሰስና ወንዞች ዳርቻ አካባቢ ለአደጋ ስጋት ባለው ቦታ የሚኖሩ እና እንዲዛወሩ ሲጠየቁ ተባባሪ አለመሆን፣

2. የወንዞችን ፍሰት የሚቀይሩና ለአደጋ የሚያጋልጡ የግንባታ ተረፈ ምርቶች" አፈርና የተለያዩ ቆሻሻዎች በወንዞች ውስጥ መድፋት"

3. በመንገድ ቦዮች ውስጥ ቆሻሻ በመድፋት ቦዮች በመደፈናቸው ምክንያት በህይወትና ንብረት ላይ አደጋ ሊያስከትል የሚችል ጐርፍ የሚከሰት በመሆኑ ምክንያትና የጐርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦች እንዳሉ በመረዳት የከተማው አስተዳደር ከወዲሁ ችግሮቹን ለመቅረፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ሁሉም የከተማችን ነዋሪዎች እና በተለይም ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተማችን የጎርፍ አደጋዎች እንዳይከሰት በህይወትና ንብረት ላይ ጉዳቶች እንዳይደርስ ከተማ አስተዳደሩ ከሚሰራው የጎርፍ አደጋ መከላከል ስራ በተጓዳኝ ነዋሪያችን የቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ ይጠበቅበታል። በዚህም መሰረት በዘንድሮው ክረምት ያልተጠበቁ አካባቢዎች ጭምር አደጋ እንዳያጋጥም ሁሉም የከተማችን ነዋሪዎች የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች እንዲያደርጉ ፡-

1. በየአካባቢያችን የሚገኙ ለጐርፍ አደጋ ስጋት የሆኑ በቆሻሻ የተደፈኑ የፍሳሽ መውረጃ ቱቦዎችን በመጥረግ እና በማፅዳት"

2. ወደ ወንዞችና የውሃ መውረጃ ቱቦዎች ቆሻሻ የሚጥሉ ህገወጥ የሆኑ አካላትን በመከላከልና በማጋለጥ"

3. ለጉርፍ ተጋላጭ የሆነ አካባቢ ላይ የሚኖሩ ተነሽ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ከከተማው አስተዳደር ጐን በመቆምና በመተባበር "

4. ማንኞውም የህብረተሰብ ክፍል የሰውን ህይወት እና ንብረት ለመታደግ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በመደገፍ "

5. በተለይም ወጣቶች እነዚህ የአደጋ ስጋት የተለዩ አካባቢዎችን የዘንድሮ ጎርፍ በህይወት እና በንብረት ላይ እንዳያመጣ የበኩላቸውን በማድረግ"

6. ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በየእለቱ የሜትሮሎጂ ትንቢያን በሚዲያ በመከታተል ህይወቱንና ንብረቱን ከጉርፍ አደጋ መከላከልና መጠበቅ እንዲችል የከተማው አስተዳደር ጥሪውን ያስተላልፋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ

ሰኔ 04/ 10/ 2014 ዓ.ም

 

 

Share this Post