08
Jun
2022
ግንቦት 30 ቀን 2014 (አዲስ አበባ ኮሚዩኒኬሽን )የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ መደረጉን ገለፀ፡፡
የታሪፍ ማሻሻያው የተደረገው ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ማዕከል ያደረገ መሆኑን ቢሮው ተናግሯል ።በመዲናዋ በሚገኙ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ላይ የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ይርጋለም ብርሀኔ ናቸው።የነዳጅ ዓለም አቀፍ ጭማሪን ታሳቢ በማድረግ የትራንስፖርት አገልግሎት ዋጋ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ከ0.50 ሳንቲም እስከ 3 ብር 50 ሳንቲም የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።በሚድ ባስ 0.50 ሳንቲም እስከ 2.00 ብር ጭማሪ የተደረገ ሲሆን በሚኒ ባስ 0.50 እስከ 3.50 ብቻ የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን ጨምሮ ገልጿል ።
ህብረተሰቡ ከሰኔ አንድ ጀምሮ ተግባራዊ በሚደረገው የክፍያ ታሪፍ በላይ የሚጠይቁ ህገ ወጥ አካላትን ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸው ጥሪ አስተላልፏል ፡፡