አዲስ የስራ ባህልና ውጤታማነት!!

 

በልደታና ክ/ከተማ ከተጀመረ 29ኛ ቀኑን የያዘው የG+11የመኖሪያ ቤት ግንባታ በተቀመጠለት ጊዜ በጥራትና በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ግንባታው የደረሰበትን ደረጃ ዛሬ ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ከንቲባዋ ለግንባታው መጀመር የመሰረት ድንጋይ ካስቀመጡ ጀምሮ በተቀመጠለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በየጊዜው በልዩ ሁኔታ ክትትልና ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።

የህንፃው ብዛት አራት ባለ 11 ወለል ነው።

ከተጀመረ 29 ቀናትን የያዘ ህንፃው ካለምንም ረፍት በቀን 24 ስዓት፣ በሳምንት 7 ቀናትና በወር 30 ቀናት እየተሰራ ይገኛል።ለግንባታውም ዘመናዊ ቴክኖሎጅም አገልግሎት ላይ ውሏል።

ህንፃው ሲጠናቀቅም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን የቤት ችግር ያቃልላል ተብሏል።

Share this Post