የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሔደ ነው

 

የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብርሩ ‘’በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ’’ በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሔደ የሚገኘው፡፡

ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ÷በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት 19 ሚሊየን ወጣቶች በ12 የስምሪት መስኮች እንደሚሳተፉ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Share this Post