በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግሮችና የመፍትሄ አማራጮች ዙርያ ምክክር ተደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግሮችና የመፍትሄ አማራጮች ዙርያ ምክክር አድርገዋል፡፡

በትናንትናው እለት በተካሄደው በዚህ ውይይት በከተማዋ ያሉ የትራንስፖርት ችግሮችን ለመፍታት ከከተማ አስተዳደሩም እንዲሁም ከሚኒስቴር መስርያ ቤቱም ተወካዮች በተገኙበት የተለያዩ የአጭርና የረጀም ጊዜ የመፍትሄ አማራጮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት በተለይ አሁን ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍ በጊዜያዊነት የፐብሊክ ባሶች ወደ ትራንስፖርት ስምሪት የሚገቡበትን የመፍትሄ አማራጭ ለመጠቀም ስምምት ላይ የተደረሰ ሲሆን የድጋፍ ሰጪ አውቶብሶችም ጉዳይ የመፍትሄው አካል እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በቀጣይ የሚተገበሩ መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጡ ዘመናዊ የከተማ ትራንስፖርት አማራጮች ላይም በሰፊው ተመክሮባቸዋል፡፡

በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ባስ አማራጮችን መጠቀም የውይይቱ አንዱ አካል እንደነበረ ተጠቅሷል ።

Share this Post