ትምህርት ቤቴን አፀዳለሁ !!!

ትምህርት ቤቴን አፀዳለሁ : ፅዱና ውብ በሆነ ከተማ እኖራለሁ!" በሚል መሪ ቃል ለ3 ወራት የሚቆይና በመላው አዲስ አበባ ከ2ሺህ ትምህርት ቤቶች በላይ የሚሳተፉበት የጽዳት መርሃ ግብር በዛሬው እለት በይፋ ተጀመረ::

የፅዳት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የተዘጋጀው የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ከትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ በመተባበር ሲሆን የፅዳት ንቅናቄ ስራው ዛሬ ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ወራት እንደሚቆይ ተጠቁሟል።

ዛሬ በተጀመረው የፅዳት ንቅናቄ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ዋና ስራ አስኪያጅ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነን ጨምሮ አመራሮች : ታዋቂ አርቲስቶች : ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች : የፅዳት አምባሳደሮች : የት/ቤት ርዕሳነ መምህራንና በሁሉም አካባቢ ያሉ ተማሪዎች ተሳትፈዋል።

Share this Post