23
Sep
2022
በዓሉ በድምቀት እንዲከበር ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በመተባበር በንቃትና በትብብር እንዲንቀሳቀስ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋዊ ማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፡- "በዓለም ደረጃ ኢትዮጵያን ካስተዋወቋትና የስበት ማእከል እንድትሆን ካደረጓት ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል አንዱ የመስቀል በዓል ነው በመሆኑም ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ በርካታ ቱሪስቶችና ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችም ይታደሙበታል ነው ያሉት፡፡የዘንድሮውን የመስቀል በዓል የምናከብረው ሃገራችን ሳትወድ ተገዳ ወደ ጦርነት በገባችበትና ብዙ ጫናዎች እየተደረጉበት ባለበት ወቅት ቢሆንም፣ በዓሉን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ ድምቀቱን፣ እሴቱንና ውበቱን በጠበቀና ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን በሚያሳይ መልኩ ልናከብር ይገባል ብለዋል፡፡
በግንባር ሽንፈት የደረሰባቸው ፀረ ሰላም ሃይሎችና ተላላኪዎቻቸው በአሉን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በተለይ በአዲስ አበባ ተቀናጅተው የበዓሉን ይዘትና ሃገራዊ ገፅታ ለማጠልሸት ብሎም እኩይ መልእክቶቻቸውን ለማስተላለፍ የተዘጋጁትን ሁሉ ማሳፈር ይኖርብናል ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስቀመጡት መልዕክት ፡፡