ኢሬቻ የመላው ኢትዮጵያውያን የጋራ እሴት ነው!!

 

አራተኛው የኢሬቻ ፎረም የዋዜማ ዝግጅት በአዲስ አበባ ከተማ እንደቀጠለ ነው።

በስነስርዓቱ ላይ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት ይህ ባህል ከኦሮሞ ውስጥ ይመንጭ እንጂ ስለአብሮነት የሚሰበክበት ፤ አብሮነት ከንግግር ባለፈ በተግባር የሚኖርበት መሆኑን እያሰረፀ የመጣበት ነው ብለዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች ሲናገሩ ኦሮሞ በኢሬቻ ፈጣሪን ያመሰግንበታል እንጂ ተፈጥሮን አያመልክም ብለዋል ዋቃ ኡማ ኡመማ ፤ማለት የተፈጥሮ ፈጣሪ ፤ተፈጥሮን የፈጠርክ አምላክ ምስጋና ይገባሃል፤ ውሃውን የደፈረሰውን አጥርተህልናልና እናመሰግናለን ፤እኛም ታርቀን ሰላም ሆነን፤ ገራ ቁልቁሉ ሆዳችን ንፁህ አድርገን ተሰብስበናልና እባክህ ንፁህ አድርገን ታረቀን በማለት በባህላዊ መንገድ ልመናቸውን የሚያቀርቡበት እሴት ነው ብለዋል፡፡

ይህ እሴት የመላው ኢትዮጵያውያን እሴት ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች በገዳ ስርዓት ምክንያት ከእኛም አልፎ ለዓለም ህዝብ ያስተዋወቀን ነው ብለዋል፡፡እንደ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩ በጠቅላላው የኢሬቻ በዓል ማክበር ከጀመረበት 4 ዓመት ወዲህ ባህሉን ለማሳደግና ግንዛቤ ለመፍጠር ሰፋፊ ስራዎችን መስራቱን አውስተዋል፡፡

በ5ቱም በር እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ከተማዋን በማሳመርና በማድመቅ ፤ኢሬቻ የሰላም ነው፤ የወንድማማችነት ነው በማለት ሰፋፊ ስራዎችን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ከንቲባ አዳነች በዚሁ ወቅት የከተማው ህዝብ በአሉን በድምቀት ለማክበርና እንግዶቹን ለማስተናገድ እያደረገ አስተዋፅኦ አድንቀዋል አመስግነዋል።

በዚሁ ስነስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የኦሮምያ ክልል ፕሬዘዳንት ሽመልስ አብዲሳ ከችግር ከፈተና ወደ አዲስ ተስፋ አሸጋጋሪ የሆነ ባህል ነው ብለዋል፡፡ ፈጣሪና ፍጡራንን የሚያገናኝ በዓል ነው፡፡

እንደ ፕሬዘዳንቱ ገለፃ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም የሆራ ፊንፊኔ በዓል አከባበር በጣም ስላሳመራችሁ እጅግ አድርገን እናመሰግናችኋለን ሲሉም ገልፀዋልለከተማዋም የኢኮኖሚ ምንጭ ለከተማዋ ተጨማሪ በረከት ይዞ እንደመጣ ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ የሁሉም ባህል ሲወጣ ነው ኢትዮጵያ የምትሆነው ሲሉም ገልፀዋል፡፡

Share this Post