በዋና ዋና የእቅድ ግቦቻቸው ላይ የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

 

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከሚከታተላቸው አስፈፃሚ አካላት ጋር በዋና ዋና ግቦቻቸው ላይ የስምምነት ሰነድ ተፈራርሙ ።

የግብ ስምምነቱን ያደረጉት ተቋማት የኮሚኬሽን ቢሮ፣ የሴቶች ህጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ፣የጤና ቢሮ ፣ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ፣ ትምህርት ስልጠና ባለስልጣን፣ ትምህርት ቢሮ፣ ምግብና መድሃኒትና ቁጥጥር ባለስልጣን ፣የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ፣አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ እና ምገባ ኤጀንሲ ናቸው።

ቋሚ ኮሚቴው ከሚከታተላቸው አስፈፃሚ አካላት ጋር በግቦቻቸው ዙሪያ የስምምነት ሰነድ መፈራረማችን የአስፈጻሚ አካላት ክትትል ቁጥጥርና ድጋፍ ስራውን በተሻለ ሁኔታ ለማከናወን ይረዳል ሲሉ የሴቶችና ማህበራዊ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር ተናግረዋል::

Share this Post