14
Oct
2022
3ኛው የአዲስ አበባ ምክር ቤት 2ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሂደ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያቀረቡትን የተለያዩ የሥራ ሃላፊዎችን ሹመት አጽድቋል::
በዚሁ መሰረት
1. ዶ/ር ቀነዓ ያደታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ
2. አቶ ምትኩ አስማረ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ
3. ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ
4. ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ
5. ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር
6. አቶ ጀማል ረዲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ፀድቀዋል።