እንኳን ደስ አለን!!

 

አዲስ አበባ 'በትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮግራም' ምርጥ ተሞክሮ የ8ኛው የMUFPP (Milan Urban Food Policy Pact) ግሎባል ፎረም ዘላቂ አመጋገብ እና ስነ-ምግብ ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ ሽልማት አሸናፊ ሆነች።

አዲስ አበባ ይህንን ሽልማት ያገኘቸው ጥቅምት 17/2022 (እ.ኤ.አ) በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ " "Food to Feed the Climate Justice: urban food solutions for a fairer world " በሚል መሪ ሃሳብ በተዘጋጀው የ8ኛው የMUFPP ግሎባል ፎረም መድረክ ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ133 ከተሞች ጋር ተወዳድራ በማሸነፏ ሲሆን ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር ያሸነፈች ብቸኛ የአፍሪካ ሀገር ናት ።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ሽልማቱን በተቀበሉበት ወቅት ኢትዮጵያ ቅድሚያ ለሰው የሚሰጥ ፖሊሲ በማውጣት እየተከናወነ ስላለው ሰው ተኮር ተግባራት ከMUFPP ፈራሚ ከተሞች ለመጡ ከንቲባዎች እና ተሳታፊዎች ልምድ አካፍለዋል።

በከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተመራ የአዲስ አበባ ከተማ ልዑካን ቡድን እየተካሄደ ባለው "Food to Feed the Climate Justice: urban food solutions for a fairer world " በሚል መሪ ሃሳብ በተዘጋጀው የ8ኛው የዓለም ፎረም ላይ በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ እየተሳተፈች ነው ::

Mayor Office of Addis Ababa

Share this Post