የተቀናጀ የሚድያና የኮምዮኒኬሽን ስራ ለከተማዊ የለውጥ ስራዎች አቅም መሆኑ ተጠቆመ

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በየደረጃው ከሚገኙ የዘርፉ አመራሮች ጋር አካሄደ

ቢሮው በዛሬው ዕለት የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ያደረገው የሴክተር የኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤትና ክፍለ ከተሞችን ጨምሮ ነው

በዚሁ ግምገማ ወቅት እንደተጠቆመው የተቀናጀ የሚድያና የኮምዮኒኬሽን ስራ ለከተማዊ የለውጥ ስራዎች አቅም በመሆኑ በየደረጃው የሚገኘው የሚድያ አመራር ህብረተሰቡን ባሳተፈ መንገድ ሊያከናውን እንደሚገባ ተመልክቷል።

በአንደኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ወቅት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማጉላትና ክፍተቶችን በመሙላት ህብረተሰቡን ለላቀ ልማት ማነሳሳት ይጠበቅብናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ተይባ ሎና ገልጸዋል ።

የኮሚዩኒኬሽን መዋቅሩ የተሰሩ መልካም ስራዎችን ከማስተዋወቅ በተጓዳኝ የሕዝብ ጥያቄዎች በመንግስት እንዲፈቱ አቅም በመሆን የሕዝባችንን ስነልቦናና የሚመጥን በመንግስት ላይ ያለውን እምነት የሚያጎሉ ስራዎችን መሥራት ይጠበቅበታል ሲሉ ኃላፊዋ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል ።

በአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎችና አመራሮች እንደተናገሩት ቅንጅታዊ አሰራርንና የቡድን ስራን በማጠናከር ተገቢውን ሚዛናዊ የመረጃ አገልግሎት ለሕዝብና ለመንግሥት በማድረግ ኃላፊነቱን በሚገባው ደረጃ ሊወጣ ይገባል ሲሉ አስታውቀዋል ።

የኮሚዩኒኬሽን መዋቅሩ በሕዝብና በመንግሥት መካከል ድልድይ ሆኖ ማገልገል ይጠበቅበታል ያሉት የቢሮው ምክትልና የሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መንግሥቱ ገብሬ የቡድን ሥራም ባህል ይሆነን ዘንድ ይገባል ብለዋል ።

የኮሚዩኒኬሽን መዋቅሩን በመጠቀም ሌብነትን ጨምሮ የሚያጋጥሙ የአስተዳደር በደሎችን መታገል ይጠበቅብናል ያሉት የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሰሎሞን ዲባባ ናቸው።

ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በሚመለከት ማብራሪያ የሰጡት የፕሬስ ሰክረተርያት ኃላፊ አቶ አዶኒያስ ወልደ አረጋይ በፉክክር ሳይሆን በተዋሃደ አኳኋን የኮሚዩኒኬሽን ዘርፉን በመምራት በሀሳብ ግንባታ በመልእክት ላይ ያተኮረ የሚድያ ግንኙነት ልናከናውን ብለዋል ።

በአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎችና አመራሮች እንደተናገሩት ቅንጅታዊ አሰራርንና የቡድን ስራን በማጠናከር ተገቢውን ሚዛናዊ የመረጃ አገልግሎት ለሕዝብና ለመንግሥት በማድረግ ኃላፊነቱን በሚገባው ደረጃ ልወጣ ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ።

 

 

 

 

 

Share this Post