አዲስ አበባ አለም አቀፍ ውድድር አሸነፈች!!!

እንኳን ደስ አላችሁ!!

አዲስ አበባ የበካይ ጋዝን በሚያስቀር የዘመናዊ ደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት በመዘርጋት ባከናወነችው መልካም ስራ በC40 የከንቲባዎች ፎረም አለም አቀፍ ውድድር አሸናፊ ሆነች፡፡ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በአካል ተገኝተው ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ እ.ኤ.አ ከጥቅምት 19–21 2022 በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ ከተማ እየተካሄደ ባለው የC40 የአለም ከንቲባዎች ፎረም ላይ የአየር ንብረትን የሚከላከል ተስማሚና መልሶ የመጠቀም አሰራርን የተገበረ የያዘ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት በመዘርጋት (decentralized composting and recycling) ለአረንጓዴ እና ጤናማ የከተማ ግንባታ ሂደት እና ቆሻሻን ወደ ኮምፖስት በመቀየር ለገቢ ማስገኛ ስራ በማዋልዋ ጉልህ ድርሻ በማበርከት በመልካም ተሞክሮ ተሸላሚ መሆን ችላለች፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም የነበረውን ለበካይነት የተጋለጠ አሰራር በማስቀረት በቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት የብዙዎችን ህይወት ሊታደረግ የሚችል እና በካይ (fossil) ፎሲል ጋዝ ልቀትን ያስቀረ ፤ተመልሶ በከተማ እየተከናወነ ላለው የጓሮ አትክልት ልማት ስራ ማዳበርያ ማቅረብ ያስቻለ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት መዘርጋቱ ለእውቅና እንዳበቃው ተጠቅሷል፡፡ በዚህም ስራ የበርካታ ወጣቶችን ገቢያቸውን በከፍተኛ ደረጃ ከማሳደጉም በተጨማሪ ተፈጥሮን የሚያክም ቆሻሻን ወደ ሃብትነት የቀየረ በመሆኑ ከብዙ ትላልቅ የአለማችን ከተሞች ከቀረቡ ተሞክሮዎች ጋር በመወዳደር አሸናፊ በመሆኗ ሽልማቱን ማግኘት ችላለች፡፡ የC40 የአለም ከንቲባዎች ፎረም ከተሞች የአየር ንብረት ከካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት እና ለአለም ከተሞች የሙቀት መጨመር ምክንያት ሆነው ግሪንሃውስ ጋዝ (GHG) ተፅእኖ በጋራ ለመከላከል የተመሰረተ የአለም ሀገሮች 100 ዋና ከተሞች ጥምረት የተመሰረተ ነው፡፡ አዲስ አበባ ከቀናት በፊት በተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ የእውቅና ሽልማት ማግኘቷ አይዘነጋም፡፡ ይህ ጅምር ድሉ በሁሉም መስክ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

Share this Post