"በተግዳሮቶች ውስጥ በማለፍ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅና እና ለህዝብ ጥቅም ማዋል ተችሏል"

 

ወ/ሮ ጠይባ ሎና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለቤትነት እየተገነቡ የሚገኙ የተለያዩ ለሕዝብ የላቀ ጠቀሜታ ያላቸው ፕሮጀክቶችን ከተለያዩ የሚድያ አካላት ለተውጣጡ የሚድያ ባለሙያዎች እያስጎበኘ ይገኛል ።

በጉብኝት መርሀ -ግብሩ መጀመሪያ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ጠይባ ሎና እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ፕሮጀክቶችን መጀመር እንጂ በታለመለት ጊዜ እና ሁኔታ አጠናቆ ለህዝብ ጥቅም ማዋል በእጅጉ አዳጋች ነበር ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኝነት ባለው አመራር እየተመራ በተግዳሮቶች ውስጥ ጭምር እያለፈ ልዩ ልዩ የከተማችንን ደረጃ የሚያሳድጉና ለሕዝብ የላቀ ጠቀሜታ ያላቸውን ግዙፍ ሜጋ ፕሮጀክቶች ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ግዜና ጥራት በፍጥነት እያጠናቀቀ በማስመረቅና ለአገልግሎት ክፍት እያደረገ ላይ ይገኛል ብለዋል

የዛሬው የጉብኝት ዓላማ ከተማ አስተዳደሩ የሚያከናውቸውን አጠቃላይ ግዙፍ ሜጋ ፕሮጀክቶች ሕዝብ እንዲያውቃቸውና በባለቤትነት እንዲከታተላቸው ማስቻል ነው ብለዋል ኃላፊዋ።

በዛሬው ጉብኝት በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የታላቁ ቤተመንግሥት የቅርስና የመኪና ማቆሚያ ፕሮጀክት ፣የዘውዲቱ ሆስፒታል የማስፋፍያ ግንባታ፣የትራፊክ ማኔጅመንት ፕሮጀክት ፣ዘመናዊ የሕጻናትና የወጣቶች ቲያትር ቤት፣የአርሶ አደሮች ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ግንባታና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

 

 

Share this Post