ለኤች አይ ቪ ኤድስ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ጥልቅ የሆነ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ

 

በኤች አይ ቪ ኤድስ ሜይንስትሪሚንግ አፈፃፀም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ቢሮ የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል በየደረጃ ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

አሁንም በኤች አይ ቪ ኤድስ የሚያዙ ሰዎች ቊጥር ብዙ ነው በመሆኑም በተለይ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ጥልቅ የሆነ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ በመስራት ይገባል ተብሏል።

በሽታው ሊያሳደር የሚችለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ከመቀነስ ባለፈ የበሽታው መስፋፋት ለመቀነስ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባም ተገልጿል፡፡

የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ መንገዶችን በተለይም ኮንዶምን ሁል ግዜ እና በአግባቡ በመጠቀም የበሽታውን ስርጭት መከላከል እና መቆጣጠር እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

Share this Post