"የአፍሪካ ወጣቶች የአፍሪካን መፃኢ እድል ለመወሰን በውስጣቸው ትልቅ አቅም አለ"

"የአፍሪካ ወጣቶች የአፍሪካን መፃኢ እድል ለመወሰን በውስጣቸው ትልቅ አቅም አለ" - አቶ ደመቀ መኮንን

የአፍሪካ ወጣቶች የአፍሪካን መፃኢ እድል ለመወሰን በውስጣቸው ትልቅ አቅም እንዳለ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው የአፍሪካ ወጣቶች ጉባዔ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ነው።

አቶ ደመቀ መኮንን በጉባኤው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የአፍሪካ ወጣቶች የአፍሪካን መፃኢ እድል ለመወሰን በውስጣቸው ትልቅ አቅም አለ ብለዋል።የጉባኤው አላማም ይህን ታላቅ አቅም በተሳሰረ አንድነት እንዲያወጡት ማድረግ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም አፍሪካን የበለፀገች እንዲሁም ከተፅዕኖዎች ሁሉ የፀዳች አድርጎ ለመቅረፅ የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር ያለመ ነው ማለታቸው የብልጽግና ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤና ፍልስፍና ለአዲሱ የአፍሪካ ትውልድ ማስተዋወቅና አብሮነትን ማጠናከር ዓላማው ባደረገው ጉባዔ ከ50 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ወጣት መሪዎች ተሳታፊ ናቸው።

Share this Post