01
Nov
2022
ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት እድሳቱን ጨርሶ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።
በ1927 ዓ.ም እንደተመሰረተ የሚነገርለትና በርካታ አንጋፋ ከያንያንን ያፈራው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት አሁናዊ ገፅታውን ይዞ እንዲሰራ የተደረገው በ1994 ዓ.ም ነበር።
ይህን ገፅታውን በጠበቀ መልኩ በ2013 ዓ.ም የተጀመረው የቴአትር ቤቱ የእድሳት ስራ ተጠናቆ በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።