"ዛሬ ለከተማችን አዲስ አበባ ሌላኛው ብስራተ የሆነው የወዳጅነት ፓርክ ሁለተኛው ምዕራፍ ተከፍቷል፡፡

 

የከተማ ወጣቶችና ህፃናት የሚዝናኑበት ፣ የሚማሩበት፣ በአካልም ሆነ በአዕምሮ ብቁ ሊያደርጋቸዉ የሚችል እዉቀትንና ከክህሎት የሚያገኙበት ስፍራ ነዉ።

አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና አበባ እናደርጋለን ባልነው መሰረት ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግና ከተማችንን የቱሪስት መዳረሻ በማድረግ ረገድ ይህ ፓርክ ጉልህ ሚና አለዉ።

ለዚህ ዉብ ስራ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።

የከተማችን ነዋሪዎች እናንተም ከልጆቻችሁ ጋር መጥታችሁ እንድትጎበኙ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!"

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

Share this Post