የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ ኩራት ነው" ም/ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ

 

ጥቅምት 24 “መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ሀሳብ እለቱን የሚያስታውስ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅጥር ጊቢ ውስጥ ተካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የሥራ ኢንተርፕራይዝና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በመረሀግብሩ ላይ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ ከአሸባሪው ቡድን ትንኮሳ ወቅት አንስቶ ለአገር ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት በማሰብ ያደረገውን የሰላም ጥሪ ቡድኑ አሻፈረኝ በማለቱ መከላከያ ሰራዊት የተሰጠውን የሀገር ሉአላዊነትን የማስከበር ተልዕኮ ኢትዮጵያን አሸናፊ በሚያደርግ መልኩ በድል ፈጽሟል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ከአክሱም ዘመነ መንግሥት አንስቶ ጠንካራ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የመመስረት ሀገራዊ ትልም የነበረ ቢሆንም፣ ጥቅምት 15/1900 ግን ሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በሚንስቴር ደረጃ በአዋጅ ያቋቋመችበት አመት በመሆኑ ከሰሜን እዝ ጥቃት ጋር በጣምራ የሚታሰብ መሆኑን ምክትል ከንቲባው ገልጸዋል ።

ሽብርተኛው ኃይል ጥቅምት 24/2013 አቅም በፈቀደው ሁሉ የትግራይን ሕዝብ በሚያገለግለው በሀገሩ መከላከያ ሰራዊት ላይ በክህደት የከፈተው ጦርነት መቼም የሚዘነጋና የሚረሳ አይደለም ያሉት ም/ከንቲባው ትውልድ ዕለቱን በታሪክ ሲያስታውሰው ይኖራልም ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል ።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሉአላዊነታችን የመጨረሻ ምሽግና ብሄራዊ ዋስትናችን ነው ብለን ስንዘክር ክህደት የተፈጸመበትን የሰሜን እዝና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለአገር ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት ለሚያደርገው ሁሉን አቀፍ ተጋድሎ ሁሉ እውቅና በመስጠት ነው ሲሉ አብራርተዋል ም/ከንቲባው ።

ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ጀግንነቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲያስመሰክር ለረዳችሁ የኢትዮጵያ ሕዝቦችን በሙሉ ኢያመሰገንን ድጋፋችሁ ለወደፊቱም በዘላቂነት ሰራዊቱ በሚፈለገው መልኩ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና መደገፍ እንዲችል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ እናደርጋለንም የሚል መልዕክት ምክትል ከንቲባው አስተላልፈዋል ።

May be an image of 5 people, people standing, outdoors and tree

 

May be an image of one or more people, people sitting, people standing, crowd and outdoors

 

 

 

 

 

 

Share this Post