ቢሮው ጥቅምት 24 የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ የተጠቃበትን ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች አስበ ውሏል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከከተማው ወጣቶች፣ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት፣ ከጥንታዊ የኢትዮጵያ አባት አርበኞች፣ ከአንጋፋ አትሌቶችና ከስፖርት ቤተሰቦች ጋር መቼም አንረሳውም በሚል መሪ ሀሳብ የጥቅምት 24ቱን ጥቃት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች አስቦ ዋለ።
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብረሃም ታደስ በመክፈቻ ንግግራቸው የእናት ጡት ነካሾች በሰሜን ዕዝ አባላት ላይ ጥቃት ያደረሱበት ዕለትን በሃዘን ብቻ የምናስታውሰው ማሕጸነ ለምለም የሆነችው ኢትዮጵያ በጀግና ልጆችዋ ታላቅ ድልን በተግባር ያረጋገጡበት ወድቆ መነሳትን ለአለም ያሳዩበት ዕለት በመሆኑ በኩራት እናከብረዋለን ብለዋል።
በአድዋ ድል ዓለም ላይ ታሪክ ጽፈናል በሱማሌ ጦትነት የካራ ማራ ድል ለጀግንነታችን ምስክር ነው አሁን ኢትዮጵያ የማትደፈር መሆኗን በተግባር ተመስክሯል ያሉት አቶ አብረሃም ያልሸነፍ ባይነት መንፈስ የተላበሰው የአገር መከላልከያ ሰራዊት ትላንት በዓለም አደባባይ ያገኘነው ድል የጀግና ሰራዊት ውጤት መሆኑን ሲሉ እውቅና ሰጥተዋል።
ወጣቱ ትውልድ ከዚህ ትልቅ ትምህርት ይማር ይገባል በማለት ያሰሰቡት የተከበሩ አቶ አብረሃም አርበኞች አገር አስረክበውናል መከላከያ ሰራዊት የዘመናችን ጀግኖች አሉት ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ ያስጠሩ አንጋፋ አትሌቶች አሉን ሃገርን ማስቀጠል ሃገርን የመረከብ ኃልፊነት አለብን በዚህም የውስጥ እና የውጭ ጠላቶቻችን ማሸነፍ እንችላላን ብለዋል።
በሁሉም መስክ ውጤት ማስመዝገብ በላባችንን ድላችንን ማጽናት ይገባል ሲሉ አጽንኦት የሰጡት ቢሮ ኃላፊው ሃገራዊ ፍቅራችንን ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።