በለሚኩራ ክፍለ ከተማ እየተከናወነ ያለው የከተማ ግብርና ውጤታማ መሆኑን ተገለፀ፡፡

አርሶ አደሮች እየተገበሩት የሚገኘው የከተማ ግብርና ሰራ የኑሮ ጫናን እና የዋጋ ንረትን ለማስተካከል አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑን የክፍለ ከተማው የስራ ሀላፊዎች ተናግረዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በየደረጃው የሚገኙ የክፍለ ከተማው የመንግስት የስራ ሀላፊዎች የአርሶ አደሮችን የእርሻ ማሳ በመጎብኘት አርሶ አደሮቹ በቀጣይ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሊደረግላቸው በሚያስፈልግ ድጋፈ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

የከተማ ግብርና የህብተረሰቡን የኢኮኖሚ ጫና ከማቃለል አኳያ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው የገለፁት የለሚኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን ሮባ በቀጣይ የሰብል ምርቶችን ከማሻሻል ስራ ጎን ለጎን የወተት እና የስጋ ምርቶች ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ አክለው ገልፀዋል፡፡

በክፍለ ከተማው በዚህ በመኸር እርሻ ላይ 2075 አርሶ አደሮች 3328 ሄክታር መሬት ላይ መሰማራታቸው ተገልጿል።

 

Share this Post