ለከፈላችሁት መስዋዕትነት እናመሰግናለን፤ ሁሌም በክብር እንዘክራችኋለን !!ለከፈላችሁት መስዋዕትነት እናመሰግናለን፤ ሁሌም በክብር እንዘክራችኋለን !!

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ /ቤት አመራርና ሰራተኞች መከላከያ ሰራዊት "ጥቅምት 24 መቼም አንረሳውም" በሚል መሪ ቃል በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት የተፈጸመበትን ጥቃት አሰቡ

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ /ቤት /ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት ሁለት ዓመታት ህዝብን በማይወክሉ እብሪተኞች መከላከያ ሰራዊታችንን በመውጋት የጀመሩት ጦርነት በጀግኖቻችን የህይወት መስዋዕትነት እና በህዝባችን የገንዘብ፣ የጉልበት፣ የእውቀትና የላብ መስዋዕትነት ተቀልብሶ ትናንት ለተገኘው የሰላም ድል መብቃታችንን አስረድተዋል።

ከአራቱም ማዕዘን የተሰባሰቡት የመከላከያ ሰራዊት አባላትና ሌሎች የፀጥታ ሀይሎች በተደራጀ መልኩ በቆራጥነት በመንቀሳቀስ ዓላማቸውን በህይወት መስዋዕትነት እያሳኩ መሆኑን የገለፁት አቶ አለማየሁ ሁሉም በየተሰማራበት በቅንነትና በታማኝነት ተግቶ በመስራት የህይወት ዋጋ የተከፈለላትን ኢትዮጵያን ማስቀጠልና ማበልፀግ እንደሚገባው አሳስበዋል።

Share this Post