05
Nov
2022
የግል ባለሃብቱ በተዘረጋው የቤት ልማት የተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ በመሳተፍ ተደራራቢ የቤት ጥያቄዎችን ለማቃለል የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊያበረከት ይገባል፡፡
በዛሬው እለት በሳኩር ሪልስቴት 116 ቤቶች እንዲሁም በአልሳም ግሩፕ የተገነቡ 360 ቤቶች በተጨማሪም የንግድ ሱቆችን ጨምር ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን ቤቶች ተገኝተን አስመርቀናል፡፡
ዛሬ የመረቅነው የቤት ግንባታ በቦታ አጠቃቀም፣ በዘመናዊነት፣ በጥራት የከተማዋን ገፅታ በመቀየር፣ የአኗኗር ባህልን በማሻሻል፣በስራ እድል ፈጠራ የራሱ የሆነ ሚና ያለው ነው፡፡
ከተማችንን እንደ ስሟ ውብና አዲስ፣ ለነዋሪዎቿ የተመቸች እናደርጋለን ብለን ስንል ከተማችንን በማደስ ሂደት የግል ሴክተሩ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ አሁንም በተለያዩ የቤት አቅርቦት ሞዳሊቲዎች እንድትሳተፉና ከመንግስት ጎን ሆናችሁ ከተማችሁን እንድታለሙ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ