ዛሬ ክብርት ፕረዚዳንት ሳህለወርቅ በታደሙበት የ"ሌማት ትሩፋትን "በአዲስአበባ ተግባራዊ ለማድረግ አስጀምረናል።

በሃገር ደረጃ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ያስጀመሩትን "የሌማት ትሩፋትን " ተግባራዊ ለማድረግ በእርግጥም እውነተኛና ነፃ ሃገር፣ ብሎም ሁሉም ዜጋ የለመለመ ማእድ እና ለጎረቤት የሚተርፍ ገበታ እንዲኖረው ያለውን ራዕይ እውን ለማድረግ እልህ ገብተን በትጋት ማሳካት ይኖርብናል፡፡

በስንዴና በአረንጓዴ አሻራ ያሳካነውን በወተት በዶሮ እርባታ በማር እና በአትክልትና ፍራፍሬ የምግብ ዋስትና የማረጋገጥ ግብ እውን በማድረግ ዜጎቻችን ሌማታቸው የሚትረፈረፍ ለብዙ ወገኖቻችንም የስራ እድል እንዲፈጠር ብሎም የኢኮኖሚ ሉአላዊነታችን በድህነት አንገት ከምንደፋበት ዘመን ቀና ብለን በኩራት የምንኖር እውነተኛ ነፃ ህዝቦች ያደርገናል፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ!

አመሰግናለሁ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Share this Post