"ስንተባበር እንችላለን! ስንቀናጅ ከፍ እንላለን!!

በዛሬው እለት ክብርት ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ ከተማችን አዲስ አበባ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም (Milan Urban Food Policy Pact) እና C40 በከተሞች የአየር ንብረት ጉባኤ፤ የበካይ ጋዝ ልቀትን ያስቀረ ተዘዋዋሪ ኢኮኖሚና የቆሻሻ አጠቃቀም ስርዓትን በመዘርጋት፤ መልካም ልምድ ዙርያ ያሸነፈቻቸውን ሁለት አለም አቀፍ ሽልማቶች አስመልክቶ በከተማ አስተዳደራችን የተዘጋጀውን የእውቅናና የማበረታቻ ስነስርዓት አካሂደናል፡፡

በዚህ ክቡር ስራ የተሳተፋችሁ ያገዛችሁ ያስተባበራችሁ መላው የከተማችን አመራሮችና፤ ሰራተኞች የተለያዩ ከፌደራል ጀምሮ እስከ ከተማ አስተዳደር ያላችሁ ድጋፍና ክትትል የምታደርጉ ተቋማት፤ መምህራንና ርእሰ ምህራንን፤ የትምህርት ቤት ማህበረሰብ አካላት በሙሉ ፤መጋቢ እናቶቻችን ፤የደረቅ ቆሻሻ ማሰባሰብ እና ወደ የመቀየር ስራ ላይ የተሰማራችሁ ዜጎቻችን ባለሃብቶች የግል ድርጅቶች ሌሎችም ስማችሁን ያልተጠቀሰ ሚናችሁ ያለበት አካላት በሙሉ ስላበረከታችሁት አስተዋፅኦ እናመሰግናለን።

በልዩ ሁኔታ እነዚህ ፕሮግራሞች እውን እንዲሆኑ ሃሳብ ከማፍለቅ ጀምሮ በየጊዜው ክትትላቸውና ድጋፋቸው ያልተለየን፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተራችን / ዐቢይ አሕመድ ለነበራቸው አስተዋጽኦና ተምሳሌታዊ አመራር ከልብ አመሰግናለሁ።

ሽልማቱ ስንቅም፤ ትጥቅም፤ ብርታትም ሆኖን የጀመርነውን የለውጥ ጉዞ ከብልፅግና በማድረስ የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና ክብር ለማፅናት የምንጠቀምበት ሊሆን ይገባል፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!"

ከንቲባ / አዳነች አቤቤ

Share this Post