08
Nov
2022
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልካድርን ጨምሮ የምክር ቤት አባላት እና የክፍለ ከተማው አፈ ጉባኤዎች በቅርቡ የተመረቀውን የአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየምን ጎብኝተዋል።
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና በኢትዮ ቴሌኮም የተዘጋጁ ስራዎቻቸውን እና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንት ቴክኖሎጂ የተሰማሩ የግል አልሚዎችን የፈጠራ ስራዎችን ጨምሮ ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የተሳተፉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት በሳይንስ ሙዚየሙ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን፣ የጤና ችግር ለሚገጥማቸው ሰዎች ከቤት ውስጥ ሆኖ የተለያዩ በሽታዎችን መለየትና መታከም የሚያስችሉ፣ለአፈር ምርምርና የአየር ንብረትን ለማወቅ የሚያስችሉ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የፈጠራ ስራዎችን የጎበኙ ሲሆን በተሰራው ስራ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
የሳይንስ ሙዚየሙን በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በስፋት እየተጎበኘ ነው።