የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ሙያተኞችና የሚዲያ አካላት የጉለሌ እጽዋት ማዕከልን እየጎበኙ ነው።

 

ዕፅዋት ማዕከሉ የተለያዩ ሃገር በቀል የዕጽዋት ዝርያዎች ተጠብቀው ምርምርና ጥናት የሚደረግበት ፣የዕጽዋት ናሙናዎች በቤተ መዘክር የሚቀመጡባቸውና ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፉባቸው ትልቅ ማዕከል ነው።

በከተማችን የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስፋት በርካታ ስራዎችን እየሰራ የሚገኘው የከተማ አስተዳደሩ በጉለሌ እጽዋት ማዕከል የጎብኝዎችን ቀልብ ለመሳብ የሚያስችሉ ማሻሻያዎች እየተደረገለት መሆኑን ተገልጿል ።

ማዕከሉ በቡድንም ሆነ በተናጠል ተፈጥሮን መሰረት ያደረገ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞችን ለማከናወን የሚያስችል ማዕከል ነው።

ገለሌ ዕጽዋት ማዕከል 705 ሄክታር የሚሸፍን ከመሆኑም በላይ በስፋቱ ከአፍሪቃ ትልቁ የዕጽዋት ማዕከል ሲሆን አለም አቀፍ ደረጃዎችን የሚያሟላ የዕጽዋት ማዕከል እንዲሆን ለማስቻል በርካታ መሰረተ ልማቶች በዘላቂነት እየተዘረጉለት መሆኑን የማዕከሉ ሃላፊዎች ተናግረዋል።

ዕጽዋት ማዕከሉ 2350-2950 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ከፍታ ላይ ይገኛል። ማዕከሉ የሚያገኘው የዝናብ መጠን 1100-1300ሚሊ ሜትር ሲሆን የሙቀት መጠኑ ደግሞ 15 ድግሪ ሴንትግሬድ እስከ 18 ድግሪ ሴንትግሬድ ነው ።

ጉብኝቱን የአዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ከጉለሌ እጽዋት ማዕከል በጋራ የተዘጋጀ ነው ::

Share this Post