የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሄዱ።

የመወያያ ሰነዱም በዋናነት በሰላም የተገኘውን ድል በላብ ማፅናት ፣በምግብ ዋስትና ራስን ለመቻል የከተማ ግብርናን ከሌማት ትሩፋት ተልዕኮ ጋር በማስተሳሰር ለስኬት መረባረብ በሚያችሉ አጀንዳዎች ሲሆኑ የሀገራችን ፈተና የሆነውን የዋጋ ግሽበትን መከላከል ለሠላም ስምምነቱ ተፈፃሚነት መረባረብ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ዙሪያ ከነዋሪው ጋር ውይይት ተደርጓል።

ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማጠቃለያው እንደተናገሩት ሠላም ሲኖር ነው ያሰብነውን የምናሳካው፣ሠላም ሲኖር ነው ሀገራችንን የምናበለፅገው በሠላም ያስመዘገብነውን ድል በኢኮኖሚው ዘርፍ በማፅናት ሀገር መገንባት ያስፈልጋል ሲሉ በኩታ ገጠም የተዘሩ አዝዕርቶችን ይበልጥ በማስቀጠል በምግብ ራስ የመቻል ስነልቦናን ማዳበር፣ከምንግዜውም በላይ ደግሞ ከሌማት ቱርፋት ስራዎች አንጻር ልዩ ትኩረት ሠጥቶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን አክለውም በክፍለ ከተማው እየተከናወኑ ያሉ የሌማት ትሩፋት የሆነው የሠብል ምርቶችን ለማስፋት አርሶአደሩን ማገዝ እንዲሁም 90 ቀን የሚተገበሩ ተግባራትን ልዩ ክትትል በማድረግ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

 

Share this Post