የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በሲሚንቶ ስርጭትና ቁጥጥር ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሄደ ።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስተር ፣ከንቲባ /ቤት፣የክፍለ ከተማ ንግድ /ቤት ሃላፊዎች ፣አስገንቢ ተቋማት እንዲሁም ሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎችና አከፋፋዮች በተገኙበት በሲሚንቶ ስርጭትና ቁጥጥር ላይ ውይይት ተካሂዷል

በዉይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር /ከንቲባና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንደስትሪ ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ አሁን እየታየ ያለውን የሲሚንቶ ምርት እጥረትና የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር በዋናነት የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት መስራት መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ጃንጥራር በዋናነት የፋብሪካዎች ምርት ማሳደግና ስርጭቱ ላይ ከፍተኛ የክትትል ሥራ ሊሰራበት እንደሚገባ ገልፀዋል

አቶ አደም ኑሪ የከተማው ንግድ ቢሮ ሃላፊ በበኩላቸው ለተፈጠረው የሲሚንቶ እጥረትና አርቴፊሻል የዋጋ ንረት ምክንያት በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚፈልጉ አካላት የፈጠሩት መሆኑን ገልፀው ትልልቅ ፕሮጀክት የሚያስገነቡ ተቋማት የሚረከቡትን ሲሚንቶ በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ ያለማዋል ፣ወረፋቸው የደረሰ አከፋፋዮች ምርቱን ለመረከብ እግር የመጎተት ከፍተኛ ችግር መስተዋሉን ገልፀዋል::

በቀጣይ ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ከፋብሪካ እስከ ስርጭት ያለው ሂደት ላይ ከፍተኛ የቁጥጥር ስራ እንደሚሰራም ገልፀዋል።

በመድረኩ የተሳተፋ አካላት ለስርጭት እጥረትና ለዋጋ ንረቱ መፍትሄ ይሆናል ያሉትን ሃሳብ አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል

Share this Post