አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የከተማው የስራ ኢንተር ፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ለ35 በአካል ጉዳተኞች ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የመስሪያ ቦታ በማመቻቸት ቁልፍ አስረክቧል፡፡
በከተማው ከ400 ሺ በላይ ስራ አጥ ዜጎችን ስራ ለመፍጠር እየተሰራ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ከእነዚህ ውስጥም አካል ጉዳተኞች አሉበት እነሱን የሚመጥን የመስሪያ ቦታም ለማሰናዳት መንግስት ጥረት እያደረገ ነው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደግሞ መንገዱን በመጀመር በዛሬው እለት የመስሪያ ቦታ ለማስረከብ ባደረገው ዝግጅት ላይ ተገኝተን ደስታችሁ ተካፋይ በመሆናችን ደስተኛ ነን ብለዋል፡፡
በክፍለከተማው የቦታ እጥረት ቢኖርም ለእናንተ ይህን ቦታ ማመቻቸት በመቻሉ አንደከተማ አስተዳደር ትልቅ ክብር አለን ያሉት ምክትል ከንቲባው በተሰጣችሁ ቦታ አምራች በመሆን ቦታውን በአግባቡ በመጠቀም እራሳችሁን ልትለውጡ ይገባል ብለዋል፡፡
ከተማው ውስጥ በመስሪያ በቦታዎች ያልተገባ ልምድ አለ ያሉት አቶ ዣንጥራር ይህም ቦታውን በመስሪያነት ምነግስት ይሰsጣል የተሰጠው አካልም ለሌላ ያከራያል ያ ደግሞ የከተማዋን እድገት ከመጎተቱም በላይ ያከራየውም አካል በምንም አይጠቀምም ይህን አስተሳሰብ እናንተ ጋር ፈጽሞ መታየት የለበትም ሲሉም አፅኖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
ክፍለ ከተማው 31ሺ ስራ አጥ ዜጎችን ወደ ስራ ለማስገባት በበጀት አመቱ አቅዶ እየሰራ ነው ያሉት ደግሞ የክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ብሩክ ናቸው፡፡
ከእነዚህም ውስጥ አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ ማድረግ ስላለብን በዛሬው እለት ለ120 አካል ጉዳተኞች 20 ለሚሆኑ ደግሞ ከስደት ተመላሾች ይህን ቦታ ማመቻቸት ተችሏ ብለዋል፡፡ ክፍለከተማው የቦታ እጥረት ያለበት ቢሆንም ባለው ልክ ሁሉንም እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራም ነው ብለዋል ዶክተር ብሩክ
አካል ጉዳተኞች በከተማው በርካታ ቁጥርን የያዙ ቢሆኑም በቁጥራቸው ልክ ተጠቅመዋል አይባልም ያሉት ደግሞ የከተማው ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ለና የሺንጉስ ናቸው፡፡ አካል ጉዳተኝነት ፈጽሞ ከስራ አያግድም ያሉት ዶክተሯ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለእነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሆን ቦታ አዘጋጅቶ በዛሬው እለት ቁልፍ ለማስረከብ መብቃቱ ለለውጥ በኩል ደረጃ በማሰብ መንቀሳቀሱን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
በዛሬው እለት 34 ኢንተር ፕራይዞች 93 አንቀሳቃሾችአካል ጉዳታቸው ሳያግዳቸው ተደራጅተዋል እኛም የመስራት ፍላጎታቸውን አይተን ቦታ አመቻችተን ቁልፍ አስረክበናል ያሉት በክፍለከተማው ምክትል ስራ አስፈጻሚና የስራ ኢንተር ፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅህፈት ሀላፊ ወይዘሮ ነኢመተላህ ከበደ የተደራጁትም በቆዳ፣ በልብስ ስፌትና በአገልግሎት ላይ ይሰራሉ ብለዋል፡፡