የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአለም አቀፍ በሲ40 የከተሞች የአየር ንብረት ጉባኤ የበካይ ጋዝ ልቀትን ያስቀየረ ተዘዋዋሪ የኢኮኖሚ እና የቆሻሻ አጠቃቀም ስርዓትን በመዘርጋት የ2022 አሽናፊ መሆኗ ይታወሳል::
ይሕንኑ ምክንያት በማድረግ የከተማ አስተዳዳሩ በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ዘርፍ ተሰማርተው ውጤቱ እንዲገኝ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ የዘርፉ ተሳታፊዎች በዘርፉ ተደራጅተዉ ለሚሰሩት እውቅና መስጠቱ ይታወቃል።
ይሕ እውቅና ከተበረከተላቸው አካላት አንዱ ለሆኑት ለአቶ ሁሴን አሕመድ በተሰጣቸው እውቅና የአሜሪካ ኢምባሲ የተሰማውን ደስታ ገለፀ።
አቶ ሁሴን አሕመድ ሶይል ኤንድ ሞር ኢትዮጵያ /soil and more Ethiopia/ ድርጅት የአለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ባቋቋሙት ተቋም ሁለት ሺሕ ወጣቶችን በማሰልጠን እና በሁሉም ክፍለ ከተሞች በዘርፉ ለስራ በማሰማራት በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስራ ለብዙዎች የስራ እድል ከመፍጠር ባሻገር ከተማ አስተዳደሩ በአለም ተወዳዳሪ እና ተሸላሚም እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ተወተዋል።
ከተማ አስተዳደሩም ለአቶ ሁሴን አሕመድ እና ለመላው የተቋማቸው ሰራተኞች እንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክቱን ማስተላለፍ ይወዳል።
መትጋት፣መተባበር በጋራ መቆም ያስከብራል። ሁሉም በተሰማራበት የስራ መስክ የነ አቶ ሁሴንን መንገድ እንደ አርአያነት ቢወስድና ቢሰራ አዲስ አበባን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት የምናደርግበት ጊዜ ቅርብ ይሆናል።