"የከተማውን ፅዳት በግድየለሽነት በሚያቆሽሹ ግለሰቦች ፣ ድርጅቶችና ተቋማት ላይ ህግና ደንብን መሠረት ያደረገ የተጠናከረ እርምጃ ይወሰዳል !!"

በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሰራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ

በአዲስ አበባ ከተማ 'ከተማዬን አፀዳለሁ፤ ፅዳትን ባህል አደርጋለሁ" በሚል የቀጣይ 3 ወራት ' የፅዳት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ዛሬ በልደታ ክፍለ ከተማ ተካሄደ።

በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሰራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ የፅዳት ንቅናቄውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት ፅዳት የከተማው ባህል ሆኖ እንዲዘልቅ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በእኩል ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

አብላጫው የከተማው ነዋሪ እያፀዳ ጥቂቶች ከተማውን እንዲያቆሸሹ መፍቀድ የለብንም ያሉት አቶ ጥራቱ በየነ በቀጣይ የከተማውን ፅዳት በግድየለሽነት በሚያቆሽሹ ግለሰቦች ድርጅቶችና ተቋማት ላይ ህግና ደንብን መሠረት ያደረገ የተጠናከረ እርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቀዋል

ከተማችን አዲስ አበባ ፅዱ ውብና ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን በማድረግ ረገድ በከተማ አስተዳዳሩ እየተከናወኑ ያሉ አበረታች ተግባራት በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በባለቤትነት ስሜት የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል

በአዲስ አበባ ከተማ 'ከተማዬን አፀዳለሁ፤ ፅዳትን ባህል አደርጋለሁ" በሚል የቀጣይ 3 ወራት ' የፅዳት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ዛሬ በልደታ ክፍለ ከተማ ተካሄደ።

በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሰራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ የፅዳት ንቅናቄውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት ፅዳት የከተማው ባህል ሆኖ እንዲዘልቅ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በእኩል ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

አብላጫው የከተማው ነዋሪ እያፀዳ ጥቂቶች ከተማውን እንዲያቆሸሹ መፍቀድ የለብንም ያሉት አቶ ጥራቱ በየነ በቀጣይ የከተማውን ፅዳት በግድየለሽነት በሚያቆሽሹ ግለሰቦች ድርጅቶችና ተቋማት ላይ ህግና ደንብን መሠረት ያደረገ የተጠናከረ እርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቀዋል

አቶ ጥራቱ በየነ አክለውም የከተማው ፅዳትና ውበት መጠበቅ የሚጠቅመው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል እንደመሆኑ አካባቢያቸውን የሚያቆሸሹ ጥቂት አካለት ህብረተሰቡ ተገቢውን ግንዛቤ ከመስጠት ባለፈ አስፈላጊው ተጠያቂነት እንዲረጋገጥና ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

Share this Post