08
Jun
2022
የአዲስ አበባ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ከሚገኙ የኮሚዩኒኬሽን ተቋማት በመጀመሪያ ዙር ያሰባሰበውን ከ1 ሺህ 9 መቶ በላይ መጻሕፍት ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት አስረከበ።
ተቋሙ ድጋፍ ያደረጋቸው መጻሕፍት የታሪክ፣የልብ ወለድ፣ የሙዮኒኬሽና የህግ መጽሕፍትን ጨምሮ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው የተፃፉ ናቸው ተብሏል።
በርክክብ ስነ- ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙዮኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ እንደተናገሩት፤ ጽሓፍትን የሚያነብ ትውልድና ማህበረሰብ ሃገርን የመሻገርም ሆነ የማሻገር አቅም አለው፡፡ አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት በኢትዮጵያ የንባብ ባህል እንዲዳብር በማድረግ በምክንያት የሚያምን እና የሚጠይቅ ትውልድ ለመፍጠር ትልቅ አስተዋጽዖ ያደርጋል ብለዋል።
ተቋማቸው ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ያሚያደርገውን መጽሕፍ የማሰባሰብ ስራ በሁለተኛ ዙር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙዮኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ ተናድረዋል፡፡
በተጨማሪም የከተማችን ማህበረሰብ መጽሕፍትን ወደ አብርሆት ቤተ-መጻህፍት በማምጣት የትውልዱን የማንበብ ባህል ለማሳደግ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥሉም የቢሮ ኃላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ ጠይቀዋል፡፡