በመዲናዋ ለ10ሺህ ሴቶች የስራ ክህሎት እና የአመለካከት ስልጠና የማጠቃለያ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

 

የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ሚናዉ የጎላ ነው ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ እና የሴቶች ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ሜሮን አራጋው እንደተናገሩት የሴቶች ተጠቃሚ ለማረጋገጥ በየደረጃው ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት በመስራት የሴቶችን ተጠቃሚ ለማረጋገጥ እየሰራን ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

አክለውም ምክትል ቢሮ ሀላፊዋ ሴቶችን የሚደረሰባቸውን ፆታዊ አካላዊና ስነልናዊ ጉዳት ህግ ለመከታተል ለመደገፍ የህግ አገልግሎት በአቅራቢያቸዉ ባሉ ተቋማት እንዲያገኙ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

ስልጠና በ11ዱም ክፍለ ከተማ ለ10 ዙር ሲካሄድ የቆየው ሲሆን የወጣት ሴቶች የአመለካከት ለውጥ ፣የንግድ ክህሎትና የስራ ፈጠራ ባህልን በማሳደግ እና በገቢ ማስገኛ የስራ ዘርፎች እንዲሰማሩ ለተሰጠው ስልጠና ማጠቃለያ የውይይት ፕግሮግራም በዛሬው ዕለት በኤልያና ሆቴል ተካሄዷል፡፡

Share this Post