13
Oct
2022
የ12ኛ ክፍል የ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ ለፈተናው ከተቀመጡ 595 ሺህ ተፈታኞች ውስጥ 586 ሽህ 541 ተፈታኞች ፈተናውን ወስደዋል ብሏል።
ፈተናው በተጀመረበት ወቅት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የደረሰው አደጋ እና በአማራ ክልል በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህርዳር እና ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ስርዓቱ ባፈነገጠ ሁኔታ አንፈተንም በማለት 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው መውጣታቸውን አስታውቋል።
ከሌሎቹ በተለየ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ሃይል በተቀላቀለበት መልኩ በደረሰ ግርግር የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ በፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት መድረሱንም ነው የገለጸው ሲል ፋና ዘግቧል ።