የካቲት 12 ሜዲካል ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በህክምናው ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 77 ስፔሻሊስት ሃኪሞች እና 139 የህክምና ባለሙያዎችን አስመርቀናል።

ተመራቂዎች ከብዙ ልፋት ፣ጥረትና ውጣ ውረድ በኋላ ለስኬት በመብቃት ክቡር በሆነው ሙያ ቃለ መሀላ ገብታችሁ ወገኖቻችሁን በፍፁም ቅንነትና ታማኝነት ለማገልገል በመብቃታችሁ የተሰማኝ ደስታ ከፍተኛ ነው፤ እንኳን ደስ አላችሁ።

መዲናችን አዲስ አበባን በህክምናው ዘርፍ የቱሪዝም ማዕከል እንድትሆን ለማስቻል የተያዘው ውጥን ስኬታማ እንዲሆን እየተሰራ ያለውን ስራ የሚደግፍ ነው።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ !!

ከንቲባ / አዳነች አቤቤ

Share this Post