26
Apr
2022
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሕገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 127 የቀበሌ ቤቶች ለአቅመ ደካሞች፣ ረዳት ለሌላቸው እና ለአካል ጉዳተኞች አስረክበዋል :: ከቤቶቹ ማስረከብ በተጨማሪ ማዕድንም አጋርተዋል፡፡
የቀበሌ ቤቶቹን በማስተላለፍ መርሐግብሩ ከንቲባዋ እንደገለጹት በእንደዚህ አይነት ድሃ ተኮር ሆኑ ስራዎችን ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸው ትርጉም ትልቅ ነው ብለዋል፡፡ ስለዚህም ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
አጠገባችን ያለው ሰው ብንደግፍ ችግሮችን ማቃለል እንችላለን ብዙዎች እንደዚህ አይነት ስራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
በዛሬው እለት ርክክብ የተደረገባቸው ቤቶች የፍትሃዊ ተጠቃሚነት አንዱ ማሳያ ነው ያሉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሽታዬ መሃመድ በበኩላቸው በቀጣይም የማጥራት ስራ እየሰራን በህገወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶችን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ ነዋሪዎች የማስተላለፉ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።