በ13 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የሚሆነው የሴቶች የተሃድሶና መልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል ግንባታ ማዕከል እውነታዎች

በትናንትናው እለት በከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋ የስራ ማስጀመርያ የተከናወነው የሴቶችን ማህበራዊ ችግሮች በማቃለል ረገድ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት የሴቶች የተሃድሶና መልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል :-

👉በዓመት እስከ 10ሺህ የሚደርሱ ሴቶችን እያሰለጠነ የሚያወጣ እና 10 ዓመት ውስጥ እስከ 100ሺህ ሴቶች ሰልጥነው ለማውጣት እቅድ የተያዘለት ነው። ከስልጠና በኋላ በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም ሴቶቹ ወደየሚሰማሩበት የስራ አካባቢ የሰለጠነ የሰው ሀይል አቅርቦት ምንጭ ሆኖ የሚያገለግል ጭምር ነው።

👉የረጅም ጊዜና የአጭር ጊዜ ስልጠናዎች የሚሰጡበት ሲሆን የስነልቦናና የህይወት ክህሎት እንዲሁም የተለያዮ የቴክኒክ ስልጠናዎች ይኖሩታል።

👉ተቋሙ የስልጠና ተቋም ያለው ሲሆን ማደሪያ ወይም ዶሪሚተሪ ሕንጻ፣ 1000 ተሸከርካሪ ማቆሚያ የሚያስችል የተሽከርካሪ ማቆሚያ ፣የሕጻናት ማቆያ ፣መመገቢያ ክፍሎች መዝናናዎችና የመሸጫ ሱቆች ይኖሩታል፡፡

👉በማዕከሉ የውበት ፣የሽመና፣የሽክላ ስራ፣የኤሌክትሪክና ቧንቧ ስራ ፣የፋሺንና ዲዛይን፣የምግብና መስተንግዶ ሙያዎች ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

 

 

 

Share this Post