የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤትእና ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ሰራተኞች በጋራ 15ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅዓላማ ቀንን አከበሩ።

 

በአስራ አምስተኛው ብሄራዊ የሰንደቅዓላማ ቀን አከባበር መረሀ-ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር፥ ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በጋራ ብሔራዊ የሰንደቅ-ዓላማ ቀንን በድምቀት በጽፈህት ቤቱ ቅጥር ግቢ አክብረዋል ።

የሰንደቅ -ዓላማ ቀንን ያከበሩት ሰራተኞች ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ ለማድረግ ብሎም የሀገራችንን ብሔራዊ አንድነትና ሉአላዊነት ለመጠበቅ ልክ እንደ አባቶቻችን ገድል ለመፈፀም እኛም የዛሬ ትውልዶች ዝግጁ ነን ብለዋል ።

በመረሀ -ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዣንጥራር አባይ እንደተናገሩት በኢትዮጵያዊነታችን ጸንተን በመቆም በአንድነት በተሰማራንበት ሁሉ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን ከፍ እንዲል ልንሰራ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ።

ምክትል ከንቲባው አገራችንን በአሁኑ ወቅት ከውስጥም ከውጪም በቅንጅት እየተሰነዘረባት የሚገኝን ጥቃት በኢትዮጵያዊ አንድነትና ወንድማማችነት ስሜት ልንመክት ይገባልም ብለዋል ።የዛሬው የሰንደቅዓላማ ቀን በሁሉም ግንባር ለተሰው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የጥምር ጦር አባላት ጀግኖቻችን መታሰቢያ ይሁን የሚል መልዕክት በመርሀ -ግብሩ ማጠቃለያ ላይ ተላልፏል ።

Share this Post