የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በ2ኛ አመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

 

1. የጥቁር ህዝቦች ነፃነት እና የጀግንነት ማሳያ አርማ የሆነው የአድዋ ሙዚየም የኪነጥበብ (Art) ስራ ላይ ተወያይቶ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ተወክለው ግብአቶችን እንዲሰጡበት አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡

2. የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ የቆየውን የግንባታ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን 1044 ፕሮጀክቶች በአብዛኛው የመኖርያ ቤቶች በመሆናቸው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የግንባታ ጊዜያቸው እንዲራዘምላቸው ወስኗል፡፡

.በሌላ በኩል ቢሮ ለሌላቸው 11 ወረዳዎች በፈጣን የግንባታ ስልት 11 ህንፃዎች እንዲገነቡ ወስኗል፡፡

. የቃሊቲ ቱሉ ዲምቱ ቀለበት መንገድ ግንባታ ለማስጨረስ የኤግዚም ባንክ ብድር እስከሚለቀቅ ድረስ ከመንግስት በጀት በብድር መልክ ክፍያ እየተፈፀመ ፕሮጀክቱ እንዲጠናቀቅ ወስኗል፡፡

Share this Post