የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ20/80 14ኛ ዙር እና የ40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤት እጣ በነገው እለት ህዳር 6/2015 ዓ/ም በይፋ ስነስርዓት ያወጣል፡፡

በዛሬው እለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ 20/80 14 ዙር እና 40/60 3 ዙር የጋራ መኖርያ ቤት እጣ የማውጣት ስነስርዓት በነገው እለት ከሰዓት በኋላ 8 ሰዓት ጀምሮ እንደሚያካሂድ ተገልጿል፡፡

በመግለጫው / ያስሚን ዋሃቢረቢ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ እንደገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 1/2014 .. 20/80 14 ዙር እና 40/60 3 ዙር የእጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በይፋ ማካሔዱ አስታውሰዋል ሆኖም ባጋጠመ የወንጀል ጥቆማ መሰረት በተደረገ ኦዲት እጣው ሙሉ ለሙሉ እንዲሰረዝ ተደርጎ በጉዳዩ የተጠረጠሩ አካላትም በህግ አግባብ እንዲጠየቁ መደረጉን አንስተዋል፡፡

ይህም በጉጉት ሲጠባበቁ የነበረውን ህበረተሰብ እጅግ ያሳዘነ ቢሆንም የተሰራው ህገወጥ ተግባር ተቀባይነት የሌለውና የብዙሀኑን ጥቅም በእጅጉ የሚጎዳ ስለነበር እጣው መሰረዙ አማራጭ የሌለው እንደሆነና በተለይም ከተማ አስተዳደሩ ጉዳዩን ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣጡ ባለሙያች ክፍት አድርጎ ኦዲት እንዲደረግ መደረጉ የከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኝነት ያሳየ መሆኑን አንስተዋል፡፡

አሁንም የከተማ አስተዳደሩ በይፋ ለህዝቡ ቃል በገባው መሰረት ቤቶቹን በአጠረ ጊዜ የተፈጠሩ ችግሮቹን በሚያርም አግባብና የሴኩሪቲ ደህንነቱን በጠበቀ መልኩ የእጣ ማውጫ ሲስተሙን በማልማት የመረጃ ማጥራትና ማደራጀት ስራና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ለእጣ ዝግጁ ማድረጉን ገልፀዋል፡፡

በዚህም መሰረት በሁለቱም የጋራ መኖሪያ ቤት ፕሮግራም ማለትም 20/80 18,930 ቤት እና 40/60 6,843 ቤቶች በድምሩ 25,791 ቤቶች እጣ የሚወጣባቸው ሲሆን ቀደም ብሎ ከፍተኛ ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረውን የባለ 3 ሶስት መኝታ ቤት

ተመዝጋቢዎችን ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ 300 መቶ ቤቶችን ቀሪ ስራ በማከናወን ለነባርና አዲሰ ተመዝጋበዎች በእጣ ለማስተላለፍ ዝግጁ መደረጉን / ያስሚን ገልፀዋል፡፡

የእጣ ማውጫ ሲስተም ማልማትና ፍተሻን በተመለከተ እንደ / ያስሚን ገለፃ የቤት ዕጣ ማውጫ ሲስተሙን በአዲስ መልክ ከፍተኛ ልምድ ባለዉ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) እንዲለማ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ሲስተሙ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ ቡድን (አርተፊሻል ኢንተለጀንስ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ፣ ከከተማና መሰረተ ልማት ሚንስቴር) የተካተቱበት ቴክኒካል ኮሚቴ በድጋሚ በመፈተሽ ሲስተሙን የማረጋገጥ ስራ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት በበኩላቸው በእጣው ብቁ የሚሆኑትም 20/80 (ስቱዲዮ፣ ባለ 1 እና ባለ 2) ነባር ተመዝጋቢዎች (1997) በመመሪያው መሠረት ዝቅተኛውን 60 ወራት ቁጠባ መጠን እንዲሁም የባለ 3 መኝታ ነባርና አዲስ ተመዝጋቢዎች (2005) ዝቅተኛውን 84 ወራት ቁጠባ መጠን ያሟሉ እንዲሁም 40/60 ተመዝጋቢዎች 40% እና ከዚያ በላይ ቁጠባ ያላቸው ለእጣ ውድድር ብቁ የሆኑ እስከ የካቲት 21/2014 . ድረስ (ማለትም መረጃ መውሰጃ የመጨረሻ ቀን - cut off period) መሰረት መስከረም 9 ቀን 2015 .. ከባንክ በተገኘው መረጃ ላይ ተመስርቶ የመረጃ ማጥራት ኮሚቴው ባጠራውና ባደራጀው የመጨረሻ ሰነድ መሰረት 20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም 93,352 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም 53,540 በአጠቃላይ 146,892 ተመዝጋቢዎች ለዕጣ ብቁ ሆነው በመገኘታቸው በዚህ ዙር ዕጣ ተካትው የቤት እድለኛ ለመሆን የሚወዳደሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

Share this Post