ሴክተር መስሪያ ቤቶች የኮሚዩኒኬሽን መዋቅር የ2015 አንደኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ክትትልና ድጋፍ ሱፐርቪዥን ማድረግ ጀመረ ::

 

የሱፐርቪዥን አጠቃላይ ዋና ዓለማ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተከናወኑ ሥራዎች ይበልጥ በማጠናከር በቀጣዩ 2ኛ ሩብ ዓመት ውጤታማ ለማድረግ ነው ::

የኮሙንኬሽን ዘርፍ በሰራ ሂደት የተስተዋሉ ክፍተቶችን እየለዩ በመሙላትና በሁሉም ረገድ በተግባቦት ዘርፍ መንግስትና ሕዝብን ድልድይ ሆኖ መልካም ተሞክሮዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ማስቻል ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ በአዋጅ እንደ አዲስ ከተቋቋመበት ግዜ አንስቶ የመረጃና የግንኙነት ክፍተቶችን ለመሙላት የበኩሉን ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ከመሆኑም ባለፈ የሴክተር መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ እስከ ታችኛው እርከን ወረዳ ድረስ ያለውን የመዋቅሩን የተግባቦት ስራ አፈጻጸም በየግዜው እንደሚገመግም ይታወቃል ።

አሁን በተጀመረው በአንደኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም የዝግጅት ምዕራፍ ሱፐርቪዥን የመዋቅሩ አመራሮችና ባለሙያዎች መንግስትና ሕዝብን ድልድይ ሆኖ ከማገልገል አንጻር የተከናወኑ የተግባቦት ሥራዎችን ጨምሮ በልዩ ልዩ ሀገራዊ ጉዳይዮች ላይ ሕዝብን በማስተባበር የተከናወኑ ተግባራት የገመገማሉ ::

የሕዝብና መንግሥትን ድልድይ ሆኖ ከማገልገል አንጻር ውስንነቶች እንዳይፈጠሩ ቢሮው በዘላቂነት አመራርና ባለሙያዎቹን ማብቃትን ጨምሮ የድጋፍና ክትትል ሥራዎች አጠናክሮ ይቀጥላል።

ክትትልና ድጋፏን መሰረት አድርጉም በላቀ የሕዝብ አገልጋይነት በመፈጸም ጥቅል አበረታች አፈጻጸም ላሳዩ የመዋቅሩ አመራሮችና ባለሙያዎች ቢሮው እውቅና የሚሰጥ ይሆናል ።

Share this Post