በአዲስ አበበባ ከተማ አስተዳደር ከ246 ሺሕ በላይ በጎ ፈቃደኞችን የሚያሳትፍ የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመርያ መርሃ-ግብር ተካሄደ፡፡

2015 የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በዛሬው እለት ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋ በሚሊኒየም አዳራሽ በተለያዩ መርሃ ግብሮች አስጀምረውታል።

በከተማ አስተዳደሩ በክረምት ወቅት ሲሰሩ የቆዩ የበጎ ፈቃድ ስኬቶችን በበጋ ወቅትም ለመድገም ያስችል ዘንድ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቆ በዛሬው የበጋ በጎፈቃድ ማስጀመሪያ መርርሃግብር በይፋ ወደተግባር መገባቱን የአዲስ አበባ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንቅስቃሴ 246 ሽህ በላይ በጎ ፈቃደኞችን እንደሚያሳትፍ ተገልጿል።

በበጋው የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን 353 ሽህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚሆኑ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 3 ሺሕ ቤቶችን በማደስ አረጋውያን፣አካል ጉዳተኞችን የሀገር ባለውለታዎችን ቅድሚያ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የተገለጸ ሲሆን በዚህም ሰውን ከመደገፍ እና ከማገዝ ባሻገር 2 ቢሊየን ብር በላይ የመንግስትን ከወጪ ማዳን እንደሚቻል ተገልጿል፡፡

በስነስርቱ ማስጀመርያ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት በዚህ ስራ የምትሳተፉ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች በእናንተ እንኮራለን ብለዋል፡፡

በጎ ፍቃደኝነት አያጎድልም ያሉት ከንቲባዋ ፤ሁሉም ነገር በመንግስት በጀት ሊሰራ አይችልም ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በዚህ ስራ የምትሳተፉ ዜጎች ጉልበታችሁ ወርቅ ነው ፤በጎ አስተሳሰባችሁ ከገንዘብ በላይ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይህ ተግባር ትውልድ ይገነባል ፤ሀገር ያሻግራል ሲሉ የበጎ ፍቃድ ስራን አንድምታ ገልፀዋል፡፡

Share this Post